ስለ ተቋሙ

ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6 ሬድዮ ጣቢያ መጋቢት 23/2014 ስራውን በይፋ ጀመረ።በሚሰራቸው ዜናዎች እና ፕሮግራሞች የማህበረሰቡ ቋንቋ፣ ባህል እና ታሪክ መጎልበት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ  ማህበረሰብ አቀፍ ሚዲያ ሲሆን በዚህም በርካታ አድማጭ፣ ተመልካች እና ተከታዮችን ማፍራት ችሏል፡፡
በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች:-በፌስቡክ፣ በቲክቶክ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም እና በኦንላይን ሬድዮ አማራጮች የሚያሰራጫቸው ይዘቶች ተደራሽነትን ከተወዳጅነት ጋር ተወዳጅና ተደማጭ እንዲሆን አድርገውታል፡፡ ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6 ሬድዮ ጣቢያ በአማርኛና በስልጥኛ ቋንቋዎች ስርጭቱን እያደረገ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያትም በአለም አቀፍ እና በብሔር ብሔረሰብ ቋንቋዎች አድማጭ ተመልካቾች ጋር ለመድረስ አልሞ ይሰራል። ፈት ባድ ወገሬትን!!